መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2013-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለምአቀፍ መረጃዎች

🇺🇸በአሜሪካ በኮሮና ቫይርስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከሩብ ሚሊየን በለጠ፡፡የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ባወጣዉ መረጃ መሰረት በቫይረሱ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ250ሺ የበለጠ ሲሆን 11.5 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሆነዋል፡፡

🇺🇬እዉቁ የዩጋንዳ ሙዚቀኛ እና የፕሬዝዳንታዊ እጩ ቢቢ ዋይን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋል ባስከተለዉ ቁጣ በመዲናዋ ካምፓላ ቁጣ ተቀሰቀሰ፡፡በተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

🇨🇦ካናዳ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሳይበር ወንጀል እንዲፈፀም ድጋፍ ያደርጋሉ ስትል ቻይና፣ኢራን፣ሩሲያ እና ሰሜን ኮርያን ወነጀለች።

🇪🇬የግብፅ የሰብዓዊ መብት ዳይሬክተር በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ።በግብፅ ከ60ሺ ያላነሱ የፖለቲካ እስረኞች ይገኛሉ።

🇺🇸🇮🇱የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማይክ ፖምፒዮ በዛሬው እለት እስራኤልና ሶርያ በሚወዛገቡበት የጎላን ተራሮች ጉብኝት ያደርጋሉ።

🇯🇵በጃፓን መዲና ቶኪዮ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተሰማ።ቶኪዮ ከወራት በኃላ የኦሎምፒክ ውድድር እንደምታሰናዳ ይጠበቃል።

🇻🇳በኮሮና ቫይረስ ሊደርስ የሚችለውን የኢኮኖሚ ጉዳት ቬትናም መቋቋሟ ተሰማ።በደቡብ ምስራቃዊ እስያ ካሉ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እድገቷ በትክክለኛ ደረጃ እንደሚገኝ አይ.ኤም.ኤፍ ይፋ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *