መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2013-28 ሚሊዮን ኢትዮጲያውያን ሜዳ ላይ እንደሚፀዳዱ ተነገረ

ይህ የተባለው በዛሬው እለት ዓለም የመፀዳጃ ቤቶች ቀን በማስመልከት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በኢትዮጵያ 40 በመቶ በሜዳ የሚፀዳዱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም የመፀዳጃ ቤት ሽፋንን ወደ 70 በመቶ ከፍ መደረጉን በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

ሆኖም ግን አሁንም 28 ሚሊዮን ኢትዮጲያውያን ሜዳ ላይ እንደሚፀዳዱ በመድረኩ ተጠቁሟል።

ከሁለት ዓመት በፊት ወተር ኤድ ባወጣው መረጃ ግን በመፀዳጃ ቤት እጥረት ኢትዮጵያ ቀዳሚ ስፍራ መያዟን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

33ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በየሜዳው የሚፀዳዱ መሆኑ በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን ፤ ከአስር ኢትዮጵያዊያን ሴቶች አራቱ የጥሩ መፀዳጃ ቤት ተጠቃሚ አለመሆናቸውንም በሪፖርቱ መገለፁ አይዘነጋም።

ትዕግሥት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *