መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 12፤2013-በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በተፈፀመ የሮኬት ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች ተገደሉ።

ጥቃቱን ተከትሎ ታሊባን እጄ የለበትም ሲል አስተባብሏል።23 ሮኬቶች በከተማዋ መወንጨፉን መንግስት አስታውቋል።

የአፍጋን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ የሆኑት ታሪቅ አሪአን እንደተናገሩት ከሆነ በሮኬት ጥቃቱ ከተገደሉት አምስት ሰዎች በተጨማሪ 31 ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆነዋል።

የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ተሽከርካሪዎችና የመኖሪያ እንዲሁም የሆቴል ቤቶች መስኮትና በር ምስሎች በስፋት በማህበራዊ ገፅ ትስስር ላይ እየተጋሩ ይገኛል።

በኢራን ኤምባሲ ላይ አንዱ ሮኬት ማረፉን ምንጮቹን ጠቅሶ ሮይተርስ ፅፏል። ታሊባን ወይስ አይኤስ ሊፈፅሙት እንደሚችል የአፍጋን መንግስት ቢያሳወቅም በጥቃቱ እጄ የለበትም ሲል ታሊባንን አስተባብሏል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማይክ ፖምፒዮ በዛሬው እለት በኳታር መዲና ዶሃ ተገኝተው ከታሊባን ተደራዳሪዎች እና ከአፍጋን መንግስት ልዑክ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *