መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፣2013-አሜሪካውያን በቀጣይ ታህሳስ ወር የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሊያገኙ እንደሚችል ተነገረ

በተያዘው እቅድ መሰረት በታህሳስ ወር በታህሳስ 11 የመጀመሪያ ዙር ክትባት ለአሜሪካውያኑ እንደሚሰጥ የዩናይትድ ስቴትስ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መርሃ ግብር አስታውቋል፡፡

በአሜሪካ የመድሃኒት ኩባንያ ፊዘር እና በጀርመኑ አጋሩ በዩኤን ቴክ የተመረተው የክትባት መድሃኒት 95 በመቶ ስኬት አስመዝግበዋል፡፡

ፊዘር የተያዘው 2020 ዓመት ሳይጠናቀቅ ወይም በቀጣዮቹ 39 ቀናት 50ሚሊየን ያህል የክትባት መድሃኒት እንደሚያመርት ተሰፋ ተጥሎበት ከክትባቱ መካከል በመጀመሪያው ዙር በታህሳስ 11 አሜሪካውያኑ እንደሚከተቡ ይጠበቃል፡፡

በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ከ12 ሚሊዮን የበለጡ ሲሆን ከ 255ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *