መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2013-በሰሜን ኢራቅ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ የተሰነዘረው የሮኬት ጥቃት ከባድ እሳት ማስነሳቱ ተሰማ፡፡

በትላንተናው እለት ሰላሁዲን በተባለች ግዛት የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በነዳጅ ማጣሪያ እና ማከማቻ ላይ የተቀሰቀሰው እሳት ውድመት ከፍተኛ መሆኑ የኢራቅ የነዳጅ ሚኒስቴር አሰስታውቋል ፡፡

ጥቃቱን እኔ ነኝ የፈጸምኩት እኔ ነኝ ሲል አይ ኤስ /ዳኢሽ የተሰኘው አማፂ ቡድን አማቅ በተሰኘው ገጹ ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡

ይህ የነዳጅ ማጣሪያ ስፍራ ከዚህ ቀደም በአይኤስ ከባድ ውድመት ከደረሰበት በኋላ እ .ኤ .አ በ2017 በ ድጋሜ ተከፍቷል ፡፡ አይ ኤስ በኢራቅ መደምሰሱ የሚታወቅ ቢሆንም ቡድኑ አሁንም የሰርጎ ገብ ጥቃት መፈጸሙን ቀጥሏል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *