መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 25፤2013-በናሚቢያ የአካባቢ ምርጫ አዶልፍ ሂትለር የሚል መጠሪያ ስም ያለው ግለሰብ አሸነፈ

የናሚቢያ ፖለቲከኛ የሆነዉ አዶልፍ ሂትለር ኡኖና በሀገሪቱ በተካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በስሙ የተነሳ አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

በተወዳደረበት የምርጫ ክልል 85 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አዶልፍ ሂትለር አሸናፊ ሆኗል፡፡ሰዎች መነጋጋሪያ ቢሆኑን በእኔ ጉዳይ ስሜን ግን አልቀይርም ሲል ተደምጧል፡፡

ከጀርመኑ ጋዜጣ ቢል ጋር ቆይታ ያደረገዉ አዶልፍ ሂትለር ሲናገር የስም መመሳሰል እንዲ እኔ የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የናዚ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ አይደለሁም ሲል ተናግሯል፡፡

የጀርመን ቅኝ ግዛት በነበረችዉ ናሚቢያ አዶልፍ የሚለዉ ስም በብዛት መስማት የተለመደ ነዉ፡፡እ.ኤ.አ ከ1884 እስከ 1915 በጀርመን ቅኝ ግዛት ስር የነበረችዉ ናሚቢያ የጀርመን ደቡብ ምዕራብ አፍሪካ ተብላ ትጠራ ነበር፡፡

ከአንደኛዉ የዓለም ጦርነት በኃላ ናሚቢያ በደቡብ አፍሪካ ስር የነበረች ቢሆንም እ.ኤ.አ በ1990 ነጻነቷን አግኝታለች፡፡ሆኖም በናሚቢያ የጀርመን ቋንቋ መጠሪያ ያላቸዉ የአካባቢ ስያሜና የግለሰብ ስሞች በብዛት ይስተዋላል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *