መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 25፤2013-ባይደን አሜሪካውያን ለ100 ቀናት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ ጠየቁ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በእኔ የስልጣን ዘመን የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት አሜረካውያን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ያድርጉ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ሁሉም አሜሪካዊ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን ቢጠቀም ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ይመዘገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዉስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲደረግ ትዕዛዝ እንደሚሰጡ ባይደን ተናግረዋል፡፡በተጨማሪነትም በህዝብ ትራንስፖርት ስፍራ አፍና አፍንጫን መሸፈን የግድ እንደሚሆን አሳዉቀዋል፡፡

የፒዉ ሪሰርች ማዕከል እንዳስታወቀዉ ከሆነ 61 መቶ አሜሪካዉያን የክትባት መድሃኒት ለመዉሰድ ዝግጁ መሆናቸዉን ያስታወቀ ሲሆን በፋይዘር አማካይነት የቀረበዉ የክትባት መድሃኒት የመከላከል እቀሙ 95 በመቶ እንደሆነ መነገሩ ይታወሳል፡፡

በአሜሪካ 14.1 ሚሊየን አሜሪካዉያን በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን 276,000 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *