መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፤2013-ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጀመሪያዎቹ 100 የስራ ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን አሜሪካዊያን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መድሃኒት እንዲከተቡ እንደሚያደርጉ አስታወቁ ፡፡

ባይደን በእነዚህ 100 ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን አሜሪካዊያን የኮሮኖ ቫይረስ ክትባት እንዲወስዱ ብቻ ሳይሆን የ100 ቀናት የአፍና አፍንጫ መሸፈን መርሃ ግብርን ያስጀምራሉ ፡፡

በመላው አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ 15 ሚሊዮን በለይ ሲሆን 285ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

ባይደን ለአሜሪካ የጤና ዋና ጸሃፊነት ቦታን ለዣቬር ቤሴራ ያጩ ሲሆን የአሜሪካ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ደግሞ ሮቼል ዋለንስኪ እንደሚሾሙ ይጠበቃል ፡፡

በመጀመሪያዎቹ 100 የስራ ቀናት ኮቪድ 19 ከአሜሪካ ለማጥፋት ቃል ባልገባላችሁም ከዚህ ውጥንቅጥ እንድንወጣ ግን ማድረግ እንችላላን ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ተማሪዎችን ዳግም ወደ ትምህርት ቤት መመለስም ቀዳሚ ሰራዬ ነው ሲሉ ባይደን ተደምጠዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *