መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 1፤2013-የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ለመንግስት ባለስልጣናት ሰልፊ ፎቶ መነሳቱን ትታችሁ ስራችሁ ላይ አተኩሩ ሲሉ አስጠነቀቁ

የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ አዲስ ላዋቀሩት የሚኒስትሮች ካቢኔ ባስተላለፉት መልዕክት መሰረት ባለስልጣናት ሰልፊ መነሳት ትተው ስራቸው ላይ እንዲያተኩሩ አስጠንቅቀዋል።የስራችሁ ውጤት እንጁ በፎቶ አትናገሩ ሲሉም ተደምጠዋል።

ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ከዚህ በተጨማሪ መንግስታዊ የስራ ግንኙነቶች ሳይቀር በዋትስአፕ ግሩፕ በመፍጠር ስራን ለመስራት መሞከር ከባድ ህመም ሆኗል ሲሉም ተደምጠዋል።በዋትስአፕ የሚለቀቁ መንግስታዊ መረጃዎች ለመመዝበሩ ምክንያት ይህ ዓይነቱ አሰራር በመለመዱ ነው ብለዋል።

ጆን ማጉፉሊ 84 በመቶ የመራጮችን ድምፅ በማግኘት በወርሃ ጥቅምት ምርጫ ማሸነፋቸው የሚታወስ ሲሆን በቅፅል ስማቸው ቡልዶዘር ተብለው ይታወቃሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *