መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 2፤2013-የኬንያ የፓርላማ አባላት ለመኖሪያ ቤት አበል የተከፈላቸውን ገንዘብ እንዲመልሱ ተወሰነ

የኬንያ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለቤት አበል በሚል የተከፈላቸው ገንዘብ ህገወጥ በመሆኑ እንዲመልሱ አዟል፡፡416 ናቸው የተባሉት የምክር ቤቱ አባላት ለመኖሪያ ቤት አበል በሚል የተከፈላቸው 1.2 ቢሊየን የኬንያ ሺሊንግ ወይም 10 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

እያንዳንዱ የምክር ቤት አባል እስከ ቀጣዩ 2012 አመት ድረስ 2.8 ሚሊየን ሺሊንግ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡የኬንያ የህዝብ እንደራሴዎች በአለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ከሚባሉ የምክር ቤት አባላት መካከል ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *