መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 3፤2013-በ65 አመቷ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነችው ደቡብ አፍሪካዊት አስገራሚ ታሪክ

ኦልፋ ሴሌፔ ትባላለች ነዋሪነቷ በደቡብ አፍሪካ ሲሆን ለአመታት በአስተማሪነት አገልግላለች።በልጅነቷ በፖሊዮ የተነሳ አንድ እጇ አይታዘዝላትም።

ታዲያ ልጅ ሳለች ወላጅ እናቷ አንድ ምክርን ይለግሷት ነበር ፤”የጉልበት ስራን ለመስራት የአካል ጉዳትሽ እክል ሊሆን ስለሚችል ትምህርትሽ ላይ ትኩረት አድርጊ”የሚል ነበር።

በዚሁ ምክር በመበርታት ትምህርቷ አጠናክራ መምርህ ለመሆን በቃች።በኃላ እስከ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምርህነት ድረስ በቅታለች።

ታዲያ ውስጧ የፖፕ ሙዚቃ የመልቀቅ ፍላጎት የነበረ ቢሆንም ተቀባይነትን በቤተሰቦቿ ልታገኝ አልቻለችም።ይህንን እንዳታደርግ ልጆቿ ከመማፀን ባለፈ በወጣቶች የሙዚቃ ስልተ ምት ለመስራት ስትሞክሪ መሳቂያ ታደርጊናለች እባክሽ ሲሉ ለምነዋታል።

በድብቅ ስቲዲዮ በመግባት ሙዚቃውን ሰርታ በማጠናቀቅ በጊሲክስፋይቭ በተሰኘ የመድረክ ስም ታወጣዋለች።ይህ ዜማ ከተለቀቀ በኃላ በደቡብ አፍሪካ የሙዚቃ ቻርት መሪ ከመሆን ባለፈ ማህበራዊ ሚዲያውን ይቆጣጠራል።

ከስራ ዓለም ከተገለለች በኃላ በሙዚቃው የመጣው እውቅናዋ ለጥቂት ሳምንታት ያህል ብቻ አነጋጋሪ ቢያደርጋትም በኮቪድ 19 በተጠቃች በሁለተኛው ቀን በዚሁ ሳምንት ህይወቷ ያልፋል።

ደፋር ደግምሞ ያመነችበትን አትችይም፣አይሳካልሽም የተባለችውን መተግበሯ አድናቆት እያስገኘላት ይገኛል።

ከአካል ጉዳት ባለፈ ሴት ልጇን ከዚህ ቀደም በኤድስ ምክንያት ተነጥቃለች።ውጣ ውረድ በበዛበት በዚህ ጉዞ ግን ህልምን ለማሳካት መቼም እንደማይዘገይ አስመስክራለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *