መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2013-የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት ማክኬንዚ ስኮቲ አራት ቢሊዮን ዶላር ለምግብ ባንክ ድጋፍ ማድረጓ ተሰማ

የአለማችን ሀብታሙ ሰው እና የአማዞን ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄፍ ቤዞስ የቀድሞ ባለቤት ስኮቲ በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ገቢ ለቀነሰባቸው ሰዎች ለድንገተኛ ድጋፍ እና ለምግብ ባንክ የሚሆን ለአራት ወራት ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ገንዘቡን ከ 380 በላይ የረድኤት ድርጅቶች እንደሚደርሳቸው አስታውቃለች፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ሴቶች ይበልጥ ተጎጂ መሆናቸውን ለምግብ እጥረት መዳረጋቸውን ተናግራለች፡፡

ጥንዶቹ ከተለያዩ በኋላም በሀብት ማማ ላይ መቀጠል የቻሉ ሲሆን ስኮቲ የአለማችን 18ኛዋ ሀብታም ሴት ናት፡፡

በተያዘው ዓመት ብቻ ያላት የተጣራ ሀብት ከ 23.6 ቢሊዮን ወደ 60.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ከፍ ብሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *