መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2013-በትግራይ ክልል ሁሉን ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገለጸ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደ መደበኛ አገልግሎት አሰጣጡ ሙሉ በሙሉ ለመመለስ እየተሰራ እንዲያገኝ ተገለጸ።

በአሁኑ ወቅት ዋጃ ፣ አላማጣ ፣ ኮረም ፣ ማይጨው ፣ መሆኒ ፣ ዓዲጎሱ፣ አዲ ጉደም ፣ ኩሓ ፣ መቐለ ፣ ውቅሮ ፣ አጉላዕ ፣ ዓዲግራት ፣ ሓውዘን እና በአፋር ክልል ስር የሚገኙ በርሃሌ እና አጉላ ከተሞችም ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ፍረወይኒ ፣ ዕዳጋ ሐሙስ ፣ ዓብይ አዲ ፣ ዛላንበሳ ፣ ደውሃን ፣
የጭላ ፣ ሀገረ ሠላም እና አፅቢ በቅርብ ቀን ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ እየተሰራ
ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በትግራይ ክልል በአንዳንድ ቦታዎች በመዘዋወር የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ ምልከታ አካሂደዋል።

ቡድኑ እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም የመስክ ምልከታ ያደረገባቸው
የመቀሌ ፣ ኩሂያ ፣ ውቅሮ ፣ አጉላ ፣ ፍረወይኒ ፣ እዳጋሀሙስ ፣ ነጃሺ ፣ አዲግራት ከተሞች የሚገኙ የአገልግሎቱ ሠራተኞችና ቢሮዎችን እንዲሁም በጥገና ስራ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎችን ጭምር በመጎብኘት ከማበረታታቱ ባሻገር ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች የለየ ሲሆን በቀጣይ ሊደረጉ የሚገባቸው ድጋፎችንም መለየቱን ብስራት ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *