መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 29፤2013-በአሜሪካ ካፒቶል የተሰነዘረውን ጥቃት ያነሳሱት ትራምፕ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ኦባማ ተናገሩ


የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እንደተናገሩት በካፒቶል ለደረሰው ግጭት በህጋዊ ምርጭ ውጤት ላይ መሰረት ቢስ ውሸት በመቀጠላቸው ትራምፕ ያነሳሱት ግጭት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰተው ሁከት ለህዝባችን ትልቅ ውርደት ነው ብለዋል።የሪፓብሊካኑ ፓርቲ የባይደንን ድል ውድቅ ማድረጋቸው ያመጣው መዘዝ ነው ሲሉ ኦባማ ኮንነዋል።
የሪፐብሊካን መሪዎች የሚነድ ነበልባሉን እንዲቀጥል አልያም እንዲጠፋ ምርጫ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ቢል ክሊንተን ባራክ ኦባማ የጀመሩትን በቀውሱ ትራምፕን ተጠያቂ የማድረግ ዘመቻ ተቀላቅለዋል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ምርጫው ነፃ ነበር፤ ቆጠራው ትክክል ነበር ውጤቱ የመጨረሻው ነው ሲሉ ተናግረዋል
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *