
ቀድሞ የነበረው ጠንካራ ግንኙነት በህወሃት ከተቋረጠ በኃላ የአስመራ ህዝብ ለጥምቀት በጎንደር እንዲገኝ የተላለፈ የመጀመሪያው ጥሪ ነው።
የጋራ ባህል ያላቸው ሁለቱ ህዝቦች የጥምቀት በዓልን በጋራ ማክበራቸው በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን፣ የአንድነት ስሜት እንዲጠናከር እና በትውልዱ ዘንድ የማይበጠስ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።
በበዓሉ ጥሪ ለተደረገለት የአስመራ ህዝብም ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል።