መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-አሜሪካ የዩጋንዳ ምርጫን እንደማትታዘብ አስታወቀች

አሜሪካ በነገዉ እለት የሚደረገዉን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደማትታዘብ በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጋለች፡፡75 በመቶ የምርጫ ታዛቢዎች የእዉቅና ጥያቄ በምርጫዉ ኮሚሽን በኩል ወድቅ ተደርጓል፡፡

አምባሳደር ናታሊ ብራውን ኮሚሽኑ በርካታ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ለውሳኔው ምንም ዓይነት ማብራሪያ ሳይሰጥ ታዛቢዎችን ዉድቅ አድርጓል ብለዋል፡፡

ከአሜሪካ 88 የታዛቢዎች ቡድን አባላት የተፈቀደላቸዉ በአጋጣሚ የተመረጡ ጥቂት ታዛቢዎች ብቻ ስለመሆናቸዉ አምባሳደር ናታሊ ብራውን ተናግረዋል፡፡

የታዛቢዎች ገለል መደረግ የዩጋንዳ ምርጫ ተጠያቂነት ፣ ግልፅነት እና እምነት የጎደለው ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ለ35 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በድጋሚ በነገዉ እለት ምርጫ ከ38 አመቱ ድምጻዊና ፖለቲከኛ ቦቢ ዋይን ጋር ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡ቦቢ ዋይን ከአመታት በፊት የፍቅር ሙዚቃን ብቻ አቀንቃኝ የነበረ ቢሆንም በዩጋንዳ የጸጥታ አካላት በአንዱ ቀን ምሽት በጥፊ መመታቱ ወደ ማህበራዊ ፍትህ አንቂነት በመቀየር ወደ ፖለቲካዉ አለም ሊቀላቀል ችሏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *