መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ሀገራቸው የጦር ሃይሏን እንድታጠናክር ጥሪ አቀረቡ

የሰሜን ኮሪያ ገዢው የሰራተኛ ፓርቲ ዓመታዊ ጉባኤ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ኪም ጆንግ ኡን ሀገሪቱ የጦር አቅሟን እንድታጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጣም ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ስንገነባ የኒውክሌር ጦርነትን ለመከላከል የምንችልበት ደረጃ እንደርሳለን ሲሉ ኪም ተደምጠዋል፡፡

ሰሜን ኮርያ ረዥም ርቀት የሚጓዝ የባሊስቲክ ሚሳኤል በ 2018 ካስወነጨፈች በኋላ በድጋሚ የኒውክሌር አቅም መሸከም የሚችሉ የጦር መሣሪያዎች እንዲመረቱ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡

ደቡብ ኮሪያ የጎረቤቷን ሰሜን ኮሪያ የጦር እንቅስቃሴ እግር በእግር እየተከታተለች ሲሆን ፤ ባሣለፍነው እሁድ ወታደራዊ ትዕይንት በፒዮንግ ያንግ እንደነበረ ሴኦል አስታውቃለች፡፡

የኪም ጆንግ ኡን እህት የሆነችው ኪም ዮ ጆንግ የደቡብ ኮርያን የክትትል እርምጃ ተችታለች፡፡

ከወንድሟ ኪም ጆን ኡን በላይ ኪም ዮ ጆንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር እንዳይደረግ ጫና ታሣድራለች፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *