መደበኛ ያልሆነ

ጥር 5፤2013-ፖምፒዮ ‹‹ሞቅ ያለ ውሸት›› ዋሹ ስትል ኢራን ተናገረች

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ዋና ፀሃፊ ማይክ ፖምፒዮ ኢራን ለአልቃይዳ የሽብር ቡድን መሸሸጊያ ሆናለች ሲሉ ከሰዋል።

አልቃይዳ በአፍጋኒስታን ተራራማ ስፍራዎች ከመንቀሳቀስ ባለፈ በኢራን መንግስት እየተደገፈ ቡድኑ በኢራን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ስትል ዋሽንግተን ተናግራለች፡፡

ፓምፒዮ አልቃይዳን አስጠልላለች ሲሉ ኢራንን ይክሰሱ እንጂ በቂ ማስረጃን አላቀረቡም፡፡ የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ጆቫድ ዛሪፍ ክሱን በማስተባበል ‹‹ሞቅ ያለ ውሸት›› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ባሳለፍነው ህዳር ወር በእስራኤል የስለላ ቡድን በኢራን መዲና ቴህራን የአልቃይዳ ከፍተኛ መሪ አቡ ሙሃመድ አል ማስሪ መገደሉን ኢራን ማስተባበሏም ይታወሳል፡፡

በርካታ የአልቃይዳ ታጣቂዎች እና የኦሣማ ቢንላደን ቤተሰቦች በኢራን ተሸሽገው እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *