መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 15፤2013-የሊቢያ ተዕእኖ ፈጣሪ የሚባሉት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከግድያ ሙከራ ሴራ ማምለጣቸው ተሰማ ፡፡

በትላንትናው እለት የሊቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፋራህ ባሻሀጋህ የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቀው ወደ ትሪፖሊ ከተማ እያቀኑ በነበረበት ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቀ አደጋ ጣዮች የጥቃት ሰለባ ቢሆኑም በህይወት ተርፏል።

ከጥቃቱ በኋላ ፖሊስ ባደረገው አሰሳ ከጥቃት አድራሾች መካካል አንዱን ሲገድል ሁለቱን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡በተባባሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ለተሰጠው የትሪፖሊ መንግስት ባሻሀጋህ ከ 2018 አንስቶ የሀገር ወስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

የ58 አመቱ ባሻህጋህ ከባድ ከተባለው ጥቃት ያለ አንዳች ጉዳት መትረፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *