መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 15፤2013-ዩናይትድ አየር መንገድ 24 የቦይንግ 777 አውሮፕላኖችን ከበረራ ማገዱን አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ ሊደርስ የቻለው ባሳለፍነው ቅዳሜ በአንዱ አውሮፕላን ላይ ያጋጠመውን የሞተር ብልሽት ተከትሎ ነው፡፡የሞተር ብልሽት ያጋጠመው አውሮፕላን 231 መንገደኞችን እና 10 በረራ መስተንግዶ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር፡፡

ያጋጠመውን ችግር ተከትሎ ዴንቨር ኤርፖርት እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን በሰው ላይ ያጋጠመው ጉዳት የለም፡፡የአውሮፕላኑ አንዳንድ ክፍሎች በመኖሪያ ቤቶች ላይ መበታታኑ ተረጋግጧል፡።

ጃፓን በተመሳሳይ ቦይንግ 777 የተሰኙት አውሮፕላኖች ችግር እስኪጣራ ከበረራ እንዲታደግ ወስናለች የጃፓን ውሳኔ አምራቹ ቦይንግ የሚደገፍ ሲል ገልጾታል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *