መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 15፤2013-ዶክተር ሞሚና መሀመድ በአፍሪካ ደረጃ አሉ ከተባሉ ጥቂት የ ኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስቶች መካከል ፣የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና በማከናወን ከቀዳሚዎቹ ዶክተሮች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያውን ብሄራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ማእከል መስራችና ሜዲካል ዳይሬክተር በመሆንም አገልግለዋል ፡:

ማእከሉ ከመከፈቱ በፊት ኢትዮጵያዊያን ንቅለ ተከላውን ለማድረግ ውጭ አገር ለመሄድ ይገደዱ ነበር፡፡ ይሁንና ምስጋና ለዶክተር ሞሚና ይሁንና ማእከሉ ከተከፈተ ወዲህ በእሳቸውና በባልደረቦቻቸው አማካኝነት ወደ400 ያህል ኢትዮጵያዊያን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊደረግላቸው ችሏል፡፡ ይሁንና እኚህ ባለሙያ አሁን በአገር ውስጥ የሉም፡፡

ከጃንዋሪ 2021 አንስቶ ያገለግሉበት ከነበረው ፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሆስፒታል ፣ የብሄራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ማእከልን ለቀው ፣ የሩዋንዳውን ኪንግ ፋይሰል ሆስፒታል ተቀላቅለዋል፡፡ በመሆኑም በሩዋንዳ ለመጀመሪያ ጊዜ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና እንዲጀመር አስደርገዋል፡፡

ዶክተር ሞሚና ለሩዋንዳው ዘ ኒው ታይምስ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ በኩላሊት በሽታ ህክምና ዘርፍ ስፔሺያሊስት ለመሆን ምን እንዳነሳሳቸው ተጠይቀው ነበር፡፡

ሲመልሱም “በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የኩላሊት ስፔሺያሊት ሀኪሞች ጥቂት የነበሩ ሲሆን የኩላሊት በሽተኛው ቁጥር ግን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነበር፡፡ ስለዚህም በዋናነት የተነሳሳሁት በኩላሊት በሽታ ተይዘው በዶክተሮች እጥረት የሚሰቃዩትን ሰዎች ስቃይ ለመቀነስ በሚል ነው፡፡

ስለዚህም በውጭ አገር የተሻለና ዘመናዊ የኩላሊት ህክምና ትምህርት ተምሬ በርካታ ዶክተሮችን ለማሰልጠን ፈለኩ፡፡ በዚህ መሰረት በመጀመሪያ በደቡብ አፍሪካ ቀጥሎም በአሜሪካ የኩላሊት ህክምና ስፔሺያሊቲ ትምህርት ልከታተል ችያለሁ፡፡ ከዚያም ወደአገሬ ተመልሼ በአሜሪካ ከሚገኙ አጋሮች ድጋፍ በተደረገለት ፕሮግራም አማካኝነት የኩላሊት ህክምና ስሰጥ ቆይቻለሁ፡፡ በእነዚህ ጊዜያትም ቢያንስ 12 የኩላሊት ህክምና ስፔሺያሊስት ባለሙያዎችን ለማፍራት ችለናል” ብለዋል፡፡

Via ዳንኤል ገብረማሪያም(መዝናኛ ሚዲያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *