መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-በቅናት መንፈስ የጓደኛውን ጣት በጥርሱ ቦጭቆ የጣለው ግለሰብ በእስር ተቀጣ

ድርጊቱ ያጋጠመው ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 08፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ መስተዳድር በአባ ገዳ ክፍለ ከተማ ኦዳ ቀበሌ ልዩ ቦታው አርጋን ጠጅ ቤት አካባቢ ነው፡፡

ተከሳሽ ቢኒያም ለማ ከተበዳይ አየለ ገዛኸኝ ጋር በመጠጥ ቤቱ ውስጥ ሲዝናኑ ይቆያሉ፡፡ ይሁንና ተከሳሹ ከቆይታዎች በኋላ በሞቅታ ተበዳዩን “ለምንድነው ከእኔ ጋር የሚሄደው ጓደኛዬን የምታናግረው” በሚል በተነሳ ግጭት ከጠጅ ቤቱ ከተትሎ በመውጣት ፣ ቀኝ እጁን በመያዝ አመልካች ጣቱን በጥርሱ ቦጭቆ በመጣል ከስፍራው ሩጦ ለማምለጥ ሲሞክር በአካባቢው ህብረተሰብ በቁጥጥር ስር ይውላል፡፡

ተከሳሹን ለአባ ገዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በማስረከብ ፣ ፖሊስም ምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአዳማ ከተማ ወረዳ አቃቢ ህግ ይልካል፡፡

አቃቢ ህጉም በአካል ማጉደል ክስ መስርቶ መዝገቡን ለወረዳው ፍርድ ቤት ማቅረቡን የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ሪፓርተር ሚኪያስ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም መዝገቡን ሲመረምር ቆይቶ የካቲት 12 ቀን 2013 ዓመት በዋለው ችሎት በ 2 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *