መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-በቅዝቃዜ ወጀብ ውስጥ ባለችው የአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት የሂውስተን ከተማ ነዋሪ የነበሩት ትውልደ

ኢትዮዽያውያን እናትና የሰባት ዓመት ልጃቸው በካርቦን ሞኖኦክሳይድ በጭስ በመታፈን ህይወታቸውን አጥተዋል።

የአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት በከፋ ቅዝቃዜ ማዕበል መመታቷን ተከትሎ ባጋጠመ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት የሂውስተን ከተማ ነዋሪ የነበሩት ትውልደ ኢትዮዽያዊቷ አሜሪካዊት ወ/ሮ እቴነሽ መርሻ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ባለመኖሩ ጋራዥ ውስጥ የቆመውን መኪናቸውን ሞተር አስነስተው የእጅ ስልካቸውን ቻርጅ እያደረጉ ነበር ።

ወ/ሮ እቴነሽ የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በቤታቸው ውስጥ በሚገኝ የስልክ መስመር ከጓደኛቸው ጋር በማውራት በነበሩበት ወቅት ከመኪናቸው የሚወጣው ጭስ ወደ መኖሪያ ክፍላቸው ዘልቆ በመግባት በካርቦን ሞኖኦክሳይድ ጭስ መታፈን ሊያጋጥማቸው በመቻሉ ራሳቸውን ስተው የስልክ ግንኙነቱ ይቋረጣል፣ ባለቤታቸው በፌስቡክ ሜሴንጀር ከጓደኛቸው ጋር በፅሁፍ እያወሩ ነበር፣ በድንገት ስለተዳከሙና ስልክ መደወል እንደማይችሉ ሲረዱ፣ ለጓደኛቸው ለፓሊስ እንዲደውሉላቸው መልዕክት ላኩ።

ፓሊስ በስፍራው ሲደርስ ወ/ሮ እቴነሽና የሰባት አመት ሴት ልጃቸው ህይወታቸው አልፎ ያገኛቸው ሲሆን፣ ወንድ ልጃቸውና ባለቤታቸው ራሳቸውን ስተው በመገኘታቸው በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

በዳንኤል ገብረማርያም/መዝናኛ ሚዲያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *