መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ500ሺ በላይ ሆኖ ተመዘገበ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ የሞት መጠን በተመዘገበባት አሜሪካ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ500ሺ መብለጡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቱ ባወጣዉ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡የመጀመሪያ ሞት በካሊፍርኒያ ግዛት ከተመዘገበ ከአንድ ዓመታ በኃላ የአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 500ሺ ተሻግሯል፡፡

ከዋይት ሀዉስ ትናንትና ምሽት መልዕክት ያስተላለፉት ጆ ባይደን እንደተናገሩት ከሆነ በምድር ላይ ከሚገኙ ሀገራት ከፍተኛዉ ሞት በአሜሪካ ተመዝግቧል ሲሉ ገልጸዉታል፡፡በአንደኛዉ፣በሁለተኛዉ እና በቬትናም ጦርነት ተደምሮ አሜሪካ ካጣቸው ህይወት በላይ ቫይረሱ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ እንደነጠቃትም አንስተዋል፡፡

የባይደን አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ የቫይረሱ መዛመት በአሜሪካ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን የክትባት ሂደቱም በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የአሜሪካ የኢንፌክሽን በሽታዎች መቆጣጠር ሙሁር ዶ/ር አንቶኒዮ ፋዉቺ በቂ ቁጥር ያለቸዉ ሰዎች ክትባቱን አግኝተዋል ማለት አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዲሞክራሪክና የሪፐብሊካን አባላት ባሉበት ምክር ቤት 500ሺ አልፏል ለተባለዉ የሟቾች ቁጥር ለአፍታ ዝምታ በዛሬዉ እለት ይተገብራሉ፡፡በተመሳሳይ የፊታችን አርብ የአሜሪካ ሰንደቅ ዝቅ ብሎ እንዲዉለበለብ ዉሳኔ ተላልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *