መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በነዳጅ ላይ በሊትር የ5 ብር ጭማሪ ይደረጋል ተባለ

በኢትዮጲያ በነዳጅ ሽያጭ ላይ በሊትር እስከ ሶስት ብር ጭማሪ መደረጉ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ ይህ የዋጋ ማሻሻያ ከአለም የነዳጅ ዋጋ አንፃር የተመጣጠነ እንዳልሆነ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነዳጅ እና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሊትር ስምንት ብር ጭማሪ ማድረግ ተጠቃሚው ላይ ጫና እንዳይፈጠር በሚል መንግስት ቀሪውን ለመሸፈን መገደዱን ሃላፊው ተናግረዋል።

ይህ ሂደትም መንግስትን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረገው ተነስቷል።

በቀጣይም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እስከ አምስት ብር ጭማሪ እንደሚደረግ ሃላፊው አቶ አህመድ ቱሳ ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን አሁንም ቢሆን የማከማቻ ስፍራዎች እጥረት ፈተና ሆኗል ሲሉ አንስተዋል።

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *