መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-አሜሪካ በሁለት የማይናማር የጦር መሪዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች

አሜሪካ በማይናማር በተካሄደዉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በተሳተፉ ሁለት ተጨማሪ ጄኔራሎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታዉቃለች፡፡የአሜሪካ የግምጃ ቤት መምሪያ የውጭ ሀብት ቁጥጥር ቢሮ በትላንትናዉ እለት እንዳስታወቀው በጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፈኞችን የሆኑ ሁለት ሰዎች በመገደላቸዉ የተላለፈ እርምጃ ጭምር ነዉ ብሏል፡፡

በማይናማር የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ አንዲት የ23 ዓመት ሴት በደረሰባትት ጉዳት ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል፡፡ማዕቀቡ የተጣለባቸዉ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የአንግ ሳን ሱ ኪ መንግሥት ስልጣን አባረዉ ሀገሪቱን ለማስተዳደር በተቋቋመዉ ምክር ቤት አባል በሆኑት ሌተና ጄኔራል ሞ ሚንትን ቱን እና ጄኔራል ማውን ማውን ካው ላይ ነዉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ብሌንኬን በትዊተር ገጻቸዉ ላይ ባሳፈሩት መልዕክት አመፅ ለሚፈጽሙና ወታደራዊ አመራሮችን ተጠያቂ የሚያደርጉበት ተጨማሪ እርምጃ ነዉ ሲሉ ገልጸዉታል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *