መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013-የአደንዛዥ እጽ ዝውውር መሪ የሆነው ኢል ቻፖ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋለች

በእስር ላይ የሚገኘው የአደንዛዥ እጽ ዝውውር መሪ ኢል ቻፖ ባለቤት ኤማ ኮሮኔል አይስፕሮ ዱለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡

የ31 ዓመቷ ኤማ ኮሮኔል አይስፕሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ልትውል የቻለችዉ ኮኬን፣ማሪዋና፣ሄሮይን እና ሜታፌታሚን የተሰኙትን አደንዛዥ እጽ ለማዘዋወር ሴራ በመንደፍ ስትንቀሳቀስ ነበር በሚል ዉንጀላ ነው፡፡ባለቤቷ ኢል ቻፖ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የእድሜ ልክ እስር ተበይኖበት በኒው ዮርክ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛል፡፡

የ63 ዓመቱ ኢል ቻፖ የቀድሞው የሲናሎአ ካርቴል የወንጀል ቡድን ኃላፊ የነበረ ሲሆን በአሜሪካ ዋንኛ የአደንዛዥ እጽ ዝውውር አቅራቢ እንደሆነም ይታወቃል፡፡በቪዲዮ ኮንፍረንስ በዲሲ ማረሚያ ቤት የቀረበችው ኤማ ኮሮኔል አይስፕሮ እ.ኤ.አ ኢል ቻፖ በሜክሲኮ ማረሚያ ቤት እያለ ከእስር እንዲያመልጥ አግዛዋለች የሚል ተጨማሪ ክስ ቀርቦባታል፡፡

ኢል ቻፖ ከደሃ ቤተሰብ በሰሜን ምዕራባዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ ግዛት የተወለደ ሲሆን በመሰረተዉ የወንጀል ቡድን በርካታ ጥፋቶችን ፈጽሟል፡፡ ፎርብስ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር መረብ መሪነቱ የሚታወቀው ኢል ቻፖ የአለማችን 701ኛ ቱጃር መሆኑን ሲያሳውቅ የሀብት መጠኑም 1 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚገመት ጽፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *