መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 16፤2013 -ጥናት ሳይደረግባቸው ስራ የሚጀምሩ ማደያዎች በሀገሪቱ ለሚታየው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ሆነዋል ተባለ።

በኢትዮጲያ በተለያየ ጊዜ ለሚታየው የነዳጅ እጥረት ዘለቄታዊ መፍትሔ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ ከነዳጅ መሸጫ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሀገሪቱ ከፍተኛ ለሆነ የውጪ ምንዛሪ ብክነት እና ለኮንትሮባንድ ንግድ ተጋላጭ እንድትሆን እንዳደረጋት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነዳጅ እና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ቱሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

ጥናት ሳይደረግባቸው ስራ የሚጀምሩ የነዳጅ ማድያዎች ለብክነቱ ዋነኛ ምክንያት እንደሆኑ ተነስቷል።

የተጠቃሚ ቁጥር ከሚበዛባቸው አከባቢዎች ይልቅ ተጠቃሚ በማይኖርባቸው ስፍራዎች የሚገኙ ማድያዎች መበራከታቸው ሀገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት እንዲገጥማት እና ለኪሳራ እንድትዳረግ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።

በናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *