መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 19፤2013-ከማዘጋጃ ቤት እድሳት ጋር ተያይዞ ባጋጠመ የፊዩዝ መቃጠል ባለፉት 5 ቀናት የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እየተሰጠ አይደለም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ማዘጋጃ ቤት እድሳት ላይ መሆኑ ተከትሎ ባጋጠመ የሲስተም መቋረጥ ባለፉት አምስት ቀናት የወሳኘ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አገልግሎት ላይ መስተጓጎል ማጋጠሙን የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ አለሙ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የመረጃ ቋት ላይ በእዳሳቱ የተነሳ በደረሰበት ጉዳት አስተላላፊ ፊዮዞች ተቀጣልዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በከተማዋ የሚገኙ ወረዳዎች የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ተገደዋል ፡፡
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተቃጠሉ ፊዩዞች በመለየት ግዢ አከናውኖ በመቀየር ላይ ሲሆን አስቸኳይ ለሆኑ አገልግሎቶች የሚመጡ ተስተናጋጆች በማንዋል እንዲስተናገዱ አድርገናል ሲሉ አቶ ዮናስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በሳምንት 12ሺ በላይ የዲጂታል መታወቂያዎች ለነዋሪዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡

በቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *