መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 25፤2013-በህንድ ባል ሚስቱ ሌላ ወዳለች ሲል ለወደደችው ሰው መዳሩ ተሰማ

በህንዳ ቢሃራ ግዛት ጥንዶቹ ኡታማ እና ሳፓና በ2014 ጋብቻ ፈፅመው ሁለት ልጆችን ወልደው ለመሳም በቅተዋል።መልካም የፍቅር ዓመታት፤የሚያስቀና የትዳር ህይወት የነበራቸው ቢሆንም ይህ ግን ሊቀጥል አልቻለም።

ሚስት ሳፓና የባለቤቷ ወዳጅ የሆነው ራጁ ኩማር ወደ እነርሱ ቤት መመላለስ ሲጀምር ከእርሱ ፍቅር ይይዛታል።ከባለቤቷ ጋር ያለው ግንኙነት እየላላ ይበልጥ ከራጁ ጋር ያላቸው ፍቅር መጠናከር ይጀምራል።ትዳሯ ለመበተን የተለያዩ ድርጊቶች ሳፓና መፈፀም ትጀምራለች።

በስተመጨረሻ ትዳሩ መቀጠል እንደማይችል የተረዳው ባል ሚስቱን ለወደደችው ጓደኛው መዳሩ አነጋጋሪ ሆኗል።ቤተሰቦቿ ሳይቀር አዲሱን ትዳር ቢቃወሙም ልጆቿን ለቀድሞ ባለቤቷ በመስጠት አዲስ ህይወት ጀምራለች።

በቦሊውድ በ1999 ለእይታ የበቃ አንድ ፋልም ላይ ይህንን መሰል ታሪክ አስቀድሞ ቀርቦ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በእውን አጋጥሟል።ሳልማን ካህን
የሚተውንበት ሁም ዲል ደ ቹኪ ሳናም የተሰኘ ፊልም ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *