መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 25፤2013-በጎባ ከተማ አንዲት እናት ካርድ ላውጣ በሚል ሰበብ የ 2 ወር ጨቅላ ልጇን ጥላ ተሰወረች

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ጎባ ከተማ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ ነው፡፡

አንዲት ማንነቷ ያልተገለጸ ተጠርጣሪ የ 2 ወር ጨቅላ ህፃን ልጇን “ካርድ ላውጣ ጠብቁልኝ” በማለት ከአጠገቧ ለነበሩ ሰዎች ልጇን አስታቅፋ መጥፋቷን የባሌ ዞን ፖሊስ ኮሚዩኒኬሽን ሪፖርተር ኮማንደር ናስር ኡመር በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ የድርጊቱን ፈፃሚ በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝም ነግረውናል፡፡

ጉዳዩ የደረሰው የጎባ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤትም ጨቅላ ህፃኑን በመረከብ አሳዳጊ (ጉዲፈቻ) በማግኘቱ ማስረከቡን ብስራት ሰምቷል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *