መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 2፤2013-በሱዳን የነዳጅ ዋጋ በእጥፍ ጨመረ

ሱዳን በነዳጅ ምርቶች ከውጪ ሀገራት በሚገቡት ላይ የነበረውን ድጎማ በማንሳቷ ዋጋው በእጥፍ ጨምሯል።

ድጎማው በመነሳቱ የቤንዚን ዋጋ ከነበረበት 150 የሱዳን ፓውንድ ወደ 290 ፓውንድ ከፍ የሚል ሲሆን የናፍጣ ዋጋ በሊትር ከ125 ፓውንድ ወደ 285 ፓውንድ እንደሚጨምር የሱዳን የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ድጎማው በየአመቱ መንግስትን በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጪ ከመንግስት ካዝና እንዲያወጣ እንዳስገደደው ተገልጿል።እንዲህም ሆኖ አሁን የተደረገው ጭማሪ ሱዳን በአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ዝቅተኛ የነዳጅ ዋጋ ያለባት ሀገር ያደርጋታል።

በቅርቡ የነዳጅ ጭማሪ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳቱ አይዘነጋም።ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኃላ በተደረጉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ግሽበት ማጋጠሙ አይዘነጋም።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *