መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 2፤2013-በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የሙስና ቅሌት የተነሳ የጤና ሚኒስትሩ የስራ ፍቃድ እንዲወጡ ተደረገ

የደቡብ አፍሪካ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ዝዊሊ ሚክሂዚ በፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ግፊት በልዩ ፍቃድ ከስራ እንዲያርፉ የተደረገ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ፈንድ የሙስና ቅሌት የሀገሪቱ ዋንኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሚኒስትሩ ለሁለት የቅርብ የስራ አጋሮቻቸው ከ6 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የተመደበ ፈንድ በስራ ውል መልክ በመስጠታቸው ክስ አስነስቶባቸዋል።

ሚኒስትሩ ወረርሽኙን በመቆጣጠር ረገድ ሲሞካሹ የነበረ ቢሆንም የቀረበባቸውን ውንጀላ ይክዳሉ።ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በመንግስት የተሰጡ የስራ ውሎች በፖለቲካ ግንኙነት ላላቸው ኩባንያዎች ነው።

ከ60 በላይ የመንግስት ባለስልጣናት ከዚሁ ጋ በተያያዘ ጉዳያቸው በአቃቢ ህግ ተይዟል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *