መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 2፤2013-የአማዞን መስራቹ ጄፍ ቤዞስ እና ታዋቂ ቱጃሮች ግብር ያልከፈሉበት መረጃ አፈትልኮ መውጣቱ ተሰማ

የአለማችን ቱጃሮች ጄፍ ቤዜስ፣ኤለን መስክ እና ዋረን ቡፌት ታክስ ያልከፈሉበት መረጃ ፕሮፖብሊካ በተሰኘ የድህረ ገፅ የዜና ማጋሪያ ላይ ይፋ ሆኗል።

በመረጃው መስረት የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ በ2007 እና በ2011 ዓመት ምንም ታክስ ያልከፈሉ ሲሆን በተመሳሳይ የቴስላ ባለቤት መስክ በ2018 ዓመት ታክስ አለመክፈላቸውን ያሳያል።

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ መረጃው ያፈተለከበትን መንገድ ህገወጥ በማለት ኤፍቢአይ እና የታክስ ባለስልጣን ድርጊቱን እንደሚያጣሩት ተናግረዋል።

ፕሮፖብሊካ በበኩሉ ግን በቢሊየነሮች ግብር አከፋፈል በተመለከተ በጣም ብዙ የውስጥ መረጃዎች በሚቀጥሉት ሳምንታቶች ተጨማሪ ዝርዝሮች ይፋ ይደረጋል ብሏል።

ፕሮፖብሊካ 25ቱ የአሜሪካ ባለሃብቶች ያነሰ የግብር ክፍያ እንደሚፈፅሙ ሪፖርት አድርጓል።ከፎርብስ ባሰባሰበው መረጃ መሰረት 25ቱ የአሜሪካ ቀዳሚ ቱጃሮች ጥቅል ሀብታቸው በ2014 ከነበራቸው በ2018 ማብቂያ በ401 ቢሊዮን ዶላር ጨምሯል።

ሆኖም ግን በዚሁ ጊዜ የከፈሉት ግብር 13.6 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሀብታም አሜሪካውያንን ታክስ ለመጨመር እቅድ የያዙ ሲሆን የአሜሪካን የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማሻሻል በማለም ነው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *