መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 2፤2013-የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የጦሩ ሀላፊ በግል ጠባቂያቸው የተተኮሰባቸው ሲሆን የአፀፋውን ምላሽ ሰጥተዋል

የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የጦሩ ኃላፊ በጁባ በሚገኘው የመከላከያ ዋና መስሪያ ቤት በራፍ ላይ ከግል ጠባቂያቸው ሲተኮስባቸው የአፀፋ ምላሽ በመስጠት የተኩስ ልውውጥ አድርገዋል።

ሌተናል ጄኔራል ፒተር ዶር ማንጁር እና ሁለተኛ ሌተናል ጋትሉአክ ሪክ ከባድ ጉዳት ባይደርስባቸውም የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።የተኩስ ልውውጡ ድብቅ ሴራና አላማ ምን እንደሆነ አልተገለፀም።

የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና የተቀዳሚ ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ሀይሎች የተቀናጀ ብሄራዊ ጦር መፍጠር አለመቻላቸው እንዲህ አይነቱ ውጥረት እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል።

83ሺ ወታደሮች አሁንም ከደቡብ ሱዳን ጦር ጋር አልተቀላቀሉም።ለአምስት አመታት የዘለቀው የደቡብ ሱዳን ቀውስ እንዲያበቃ በ2018 ሁለቱ ተቀናቃኞች የደረሱበት አንዱ ስምምነት ወጥ የጦር ሀይል መመስረት ነበር።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *