መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 3፤2013-በትግራይ ክልል አርሶ አደሮች እንዳያርሱና እንዲራቡ ተደርጓል መባሉ የሀሰት ውንጀላ ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ!

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።በትግራይ ክልል አርሶ አደሮች እንዳያርሱና እንዲራቡ ተደርጓል መባሉ የሀሰት ውንጀላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

70 በመቶ የእርሻ መሬት ዝግጁ የተደረገ ሲሆን 1.2 ሚሊዮን አርሶ አደሮች ሊሰሩበት የሚችል ስፍራ መሆኑንም በመግለጫው መጠቆሙን ብስራት ሬድዮ ከአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሰምቷል።

በተያያዘ ዜና በትግራው ወቅታዊ ሁኔታ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የመንግስት ባለስልጣናትና የተባባሪ ሀገራት አምባሳደሮች ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱም በትግራይ ክልል እርዳታን ከማዳረስ አኳያ የተሰሩ ስራዎችን መካድ ከሞራልም ሆነ ከህግ አንፃር ስህተት ስለመሆኑ ተነጋግረዋል።

የዓለም አቀፍ የረድኤት ሰራተኞች ቪዛ የማራዘም ጥያቄ እየተሰራበት ሲሆን አንዳንድ የረድኤት ተቋማት የሚጠይቋቸው መሳሪያዎች አላግባብ የሆኑና የማያስፈልጉ በመሆናቸው ጥያቄው ውድቅ ተደርጓል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 60 ያህል ወታደሮች መከሰሳቸውን በዛሬው መግለጫ ተጠቅሷል።

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *