መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፤2013-የጊኒ ፕሬዝዳንት ዋንኛ ተቃዋሚ በሶስት ዓመት እስር ተቀጣ

የጊኒ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት የሀገሪቱ መንግስት ዋንኛ ተቃዋሚ በፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ላይ ተቃዉሞ እንዲካሄድ አስተባብሯል በሚል በሶስት ዓመት እስር እንዲቀጣ ዉሳኔ ተላልፎበታል፡፡

የተቃዋሚ መሪ ኦማር ሲላ ሕገ-ወጥ ስብሰባ በማካሄድ እና የሐሰት መረጃ በማሰራጨት ጥፋተኛ ተብሏል፡፡ ባለፈው 2020 ዓመት የ82 ዓመቱ አዛዉንት ፕሬዝዳንት ኮንጄ የጊኒ ህገ መንግስት በማሻሻል የስልጣን ዘመን በሁለት ዙር የሚገድበዉን አንቀጽ እንዲፋቅ አድርገዋል፡፡

በአወዛጋቢ ምርጫ በድጋሚ ቢያሸንፉም በፀጥታ አካላት በርካታ ዜጎች መገደላቸዉ ከፍተኛ ቁጣ እንደቀሰቀሰ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *