መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 15፣2013-ህውሀት የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ አፈተለከ

በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርገ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጧል።

ይሄንን ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ማዛባት።

የጦሩ ኃይል ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን ያሳያል።

ህውሀት ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል።

ህውሀት ከሰሞኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ ተሰጥቶታል።

በዚህ ትንኮሳ ወቅት ያሰለፋቸው ያልሠለጠኑ ሕጻናትና ሴቶችን መሆኑ ታውቋል።

ጁንታው ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ አስከሬኖች በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቀሌ መፈርጠጡ ታውቋል።

የደኅንነት ምንጮች እንደጠቆሙት ጁንታው በዚሁ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው ሲል የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፆ አስታዉቋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *