መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 23፤2013-በፊሊፒንስ በጎርፍ በተጥለቀለቀዉ የኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ቪዲዮ ጌም መጫውት ያላቋረጡት ወጣቶች መነጋገሪያ ሆነዋል

በፊሊፒንስ በተከታታይ ቀናት የጣለዉን ከባድ ዝናብ እና አውሎ ንፋሱ ተከትሎ እስከ ወገብ ድረስ ጥልቀት ያለዉ የጎርፍ አደጋ ያስከትላል፡፡እየጨመረ የመጣውን የውሃ መጠን ችላ በማለት የቪዲዮ ጌም አፍቃሪዎችን በፊሊፒንስ ካይኔታ ከተማ ውስጥ በኢንተርኔት ካፌ ቁጭ ብለዉ መጫወታቸዉን መቀጠላቸዉ አነጋጋሪ አድርጓቸዋል፡፡

የኢንተርኔት ካፌዉ ባለቤት ከቆይታ በኃላ አደጋዉን መገንዘብ ሲጀምር ኮምፒውተሮቹ ተዘግተው ተጫዋቾቹ እንዲሄዱ አድርጓል፡፡እንደ እድል ሆኖ ፣ በኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ያሉት የኤሌክትሪክ ኬብሎች በሙሉ ከውሃው ከፍታ በላይ ነበሩ ፣ ይህ ባይሆን ኖሮ ለቪዲዮ ጌም ያለው ከፍተኛ ፍላጎት በአሰቃቂ ሁኔታ ሊጠናቀቅ ይችል ነበር፡፡

ቪዲዮዉን ለማየት ፡-https://www.youtube.com/watch?v=8qKma3_zp78

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *