መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜን 3፤2013-ታሊባን ሴቶች ያልተካተቱበት አዲስ መንግስት መመሰረቱን አስታወቀ❗️

ታሊባን ካቡል ከተቆጣጠረ በኃላ በትላንትናው እለት እንዳስታወቀው ሟቹ የቡድኑ መስራች ሙላህ ኦማር የቅርብ ረዳት የነበሩትን ሙሃመድ ሃሰን አኩውንዳን የአፍጋኒስታን አዲስ ጊዜያዊ መሪ አድርጎ ሾሟል።በትላንትናው እለት የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቡላህ ሙጃሂድን የካቢኔው አባላትን ይፋ ያደረጉ ሲሆን የታሊባን ቀደምት አባላት አብላጫውን ቦታ ይዘዋል።

ታሊባን በመሰረተው አዲስ መንግስት ውስጥ አንድም ሴቶች አልተካተቱበትም።በኤፍ ቢ አይ የሚፈለጉትን ሳራጁዲን ሃቃኒን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው ተሹመዋል።

ሃቃኒ ኔትወርክ የተባለውን የሽብር ቡድን የሚመሩት እኚህ ሰው ከነ ቡድኑ ዋሽንግተን በጥቁር መዝገቧ ላይ አስፍራቸዋለች።የታሊባን መስራች የሟቹ ሙላህ ኦማር ወንድ ልጅ ሙላህ ሞሃመድ የመከላከያ ሚኒስትር ተደርገው ተሾመዋል።በዶሃ የታሊባን ተደራዳሪ የነበሩት አሚር ካሃን ሙታቂ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው ተሹመዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *