መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜን 4፤2013-ሱዳን እንደ ጋሪ ፈረስ የሚገፏትን አጀንዳ ይዛ አትምጣ ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ❗️

በተገባደደዉ 2013 አመት በዲፕሎማሲው ረገድ በርካታ ችግሮች ኢትዮጲያን እንደገጠማት ለጋዜጠኞች በዛሬዉ እለት ማብራሪያ የሰጡት የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ በፖለቲካ፣በዜጋ ተኮር እንዲሁም በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዙርያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ሱዳን ኢትዮጵያ ሉአላዊ መሬት ይዛ መቆየቷን በተመለከተ ችግሩ ባይፈታም ሳንዘናጋ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ስናደርግ ነበር ያሉት አምባሳደሩ የኢትዮጲያ ትዕግስት እና ጥንካሬ የታየበት ነዉ ሲሉ ሂደቱን ገልጸዋል፡፡አሁንም ቢሆን ሱዳን ይህንን ብታስብ በሰላማዊ መንገድ መጨረስ እንደምንችል መናገር እንፈልጋለን ሲሉ አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ መናገራቸዉን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል፡፡

ሱዳን ከኃላ በስውር የሚገፏትን አጀንዳ ይዛ እንደጋሪ ፈረስ አትምጣ ነው የእኛ ንግግር፤ እናስታርቃለን የሚሉ ሃገራት ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት እንድትመልስ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ተናገረዋል፡፡

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *