መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜን 5፤2013-በግርዛት ምክንያት የጨቅላ ህፃናትን ሞት በተመለከተ 37 አቤቱታዎች ደርሶኛል ሲል የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ ባለስልጣን አስታወቀ ❗️

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ከግል እና ከመንግስት የጤና ተቋማት 236 ቅሬታዎች እንደቀረቡለት አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ለብስራት ሬድዮ በላከው ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንዳመላከተው ከሆነ ፣ በወሊድ ምክንያት ያጋጠሙ የእናቶች ሞት ፣ በግርዛት ጊዜ የደረሱ የጭቅላ ህፃናቶች ሞትና እና አካል ጉዳት ዙሪያ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 236 ቅሬታዎች እንደቀረቡ ገልጿል፡፡

ከቀረቡት ቅሬታዎች መካከል የበዛ ቁጥር ያለው ቅሬታ የቀረበባቸው የግል የጤና ተቋማት ሲሆን ተቋማቱ ላይ 138 በዚሁ ዙሪያ መቅረቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል ፤ ቀሪዎቹ ቅሬታዎች የቀረበባቸው ደግሞ የመንግስት የጤና ተቋማት መሆናቸው ታውቋል ፡፡

በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በግል የህክምና ተቋማት በወሊድ ጊዜ የእናት ሞት26 ያጋጠመ ሲሆን ይህንን ቅሬታ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተቀብሎ እያጣራ እንደሚገኝ አስታውቋል 23 የመንግስት የጤና ተቋማት ደግሞ መሰሉ ቅሬታ እንደቀረበባቸው ብስራት ሬድዮ ከባለልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃው ደርሶታል።

በግርዛት ምክንያት የጨቅላ ህፃናት ሞት በመንግስት 20 በግል ደግሞ 17 ቅሬተዎችን ተቀብሎ አስተናግዷል ፡፡

156ቱ ቅሬታዎች ውሳኔ ያገኙ ሲሆን 65ቱ በሂደት ላይ ናቸው። ቀሪ 15 ጉዳዮች የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማየት ስልጣን ስለሌው ለኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ስር ለተቋቋመው የጤና ባለሙያዎች ሥነ-ምግባር ኮሚቴ መላኩን ለብስራት ሬድዮ የደረሰው ሪፖርት ይጠቁሟል ፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *