መደበኛ ያልሆነ

ጷግሜን 5፤2013-ከሰባት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባይደን እና ጂንፒንግ የስልክ ውይይት አደረጉ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአሜሪካው አቻቸው ጆ ባይደን ጋር ተነጋግረዋል። የዋይት ሀውስ መግለጫ እንዳመላከተው ሁለቱም መሪዎች ፉክክራቸው ወደ ግጭት እንዳያመራ ለማድረግ ሀገራቱ በኃላፊነት መስራት ላይ ተወያይተዋል።

ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ከጂንፒንግ ጋር ውይይት ሲያደርጉ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።የንግድ ፣ የስለላ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባሉ ጉዳዮች የዋሽንግተን እና ቤጂንግ ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች ሰፊ የስትራቴጂክ ውይይት አድርገዋል።በጋራ እና ልዩነት በሚፈጥሩባቸው ፍላጎቶቻቸው ፣ እሴቶቻቸው እና አመለካከቶቻቸው ውይይት አድርገዋል ሲሉ የዋይት ሀውስ መግለጫ አክሏል። ፕሬዝዳንት ባይደን ግልፅ እንዳደረጉት ይህ ውይይት በዩናይትድ ስቴትስ እና በቻይና መካከል ያለውን ውድድር በኃላፊነት ለማስተዳደር የአሜሪካ ቀጣይ የጥረት አካል ነው ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *