መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2014-ሰሜን ኮሪያ አብዛኛውን የጃፓን ግዛቶች መምታት የሚችል የረጅም ርቀት የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

በእረፍት ቀናቱ የተካሄደዉ ሙከራ እስከ 1,500 ኪ.ሜ መምዘግዘግ የሚችሉ ክሩዝ ሚሳኤሎች ናቸዉ፡፡የምግብ እጥረት እና የኢኮኖሚ ቀውስ ቢኖርም ሰሜን ኮርያ ግን አሁንም የጦር መሳሪያዎችን የማምረት አቅም እንዳላት ሙከራዉ ጠቁሟል።

የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራዉ ከባህር ኃይል ላይ የተደረገ ሲሆን ፒዮንግ ያንግ የመንግስትን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ የሚያስችል እና የጠላት ኃይሎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በጥብቅ ለመያዝ ይረዳል ብላለች፡፡የአሜሪካ ጦር ሙከራውን ተከትሎ ባወጣዉ መግለጫ ሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ መርሃ ግብሯን የማሳደግ ቀጣይ ትኩረት እንዳላት እና ለጎረቤቶቿ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያስከትለዉን ስጋት ያሳያል ብሏል።

የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ኃይል ከአሜሪካ የስለላ ባለሥልጣናት ጋር በጥልቀት በሙከራዉ ዙርያ ትንተና እያደረገ መሆኑን የደቡብ ኮርያ የዜና ወኪሉ ዮናሃፕ ዘግቧል፡፡የሰሜን ኮርያ የኮሚኒስት መንግስት 75 ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በፒዮንግያንግ በወታደራዊ ሰልፍ ከተካሄደ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሙከራዉ ተደርጓል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *