መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 3፤2014-በበዓል ሰሞን የባቡር አደጋን ጨምሮ ባጋጠሙ ድንገተኛ አደጋዎች የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ በበዓል ሰሞን በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።መስከረም 1 ቀን ከሀያት ወደ ጦር ሀይሎች የሚጓዝ ቀላል ባቡር ከቀኑ አስራ አንድ ሰዓት የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ዋሪት አካባቢ አጥሩን ዘሎ ለማቋረጥ ሲሞክር የነበረ የ30 ዓመት ወጣት በመግጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሚዲያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሞት የተመዘገበው በትራፊክ አደጋ ሲሆን አንዱ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ልዩ ብስራት ትምህርት ቤት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 18326 ደቡብ ህዝቦች የሆነ ዶልፊን ተሸከርካሪ ከዊንጌት ወደ አጠና ተራ ሲጓዝ የ35 ቦታውዓመት ወጣት ገጭቶ ህይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል።በልደታ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ከፍርድቤት ወደ ሜክሲኮ የሚጓዝ ተሸከርካሪ እድሜቸው 50 የሚጠጉ አዛውንት ገጭቶ ህይወታቸው ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ተናግረዋል።

በበዓሉ ዋዜማ ባልደራስ አካባቢ ከልክ በላይ በመጠጣት በተነሳ ግጭት በመዝናኛ ስፍራ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ጨምረው ነግረውናል፡፡

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *