መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 4፤2014-400 ብር የነበረው የስፖርት ውርርድ ፍቃድ ማውጫ ወደ 500 ሺህ ብር ከፍ ተደርጎ ተሻሻለ❗️

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስተዳዳሪ የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ላይ ከእዚህ ቀደም የነበሩ ህጎችን ማሻሻሉን አስታውቋል ።

አስተዳደሩ ከእዚህ ቀደም ለፍቃድ ማውጫ ይጠይቅ የነበረውን 400 ብር በተሻሻለው መመሪያ መሰረት 500 ሺህ ብር እንዲሆን መወሰኑን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር ሃላፊው አቶ ደሴ ደጀኔ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ማሻሻያ ከተደረገባቸው ህጎች መካከል የእድሳት አግልግሎት ሲሆን ከዚህ ቀደም 200ብር የነበረው አሁን 400ሺህ ብር እንዲደረግ ተወስኗል ተብሏል ።

የሽልማት ጣራው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል ።

ለውርርድ ይፈቀድ የነበረው 18 ዓመት አሁን ላይ 21 ሆኗል ተብሏል ፣ ከ21 ዓመት በታች እና የትምህርት ቤት ደንብ ልብስ የለበሱ ታዳጊዎች መጫወት እንደማይችሉ አስተዳደሩ ተናግሯል ።

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *