መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2014-ናይጄሪያ በትዊተር ላይ የጣለችውን እገዳ በቅርቡ ታነሳለች ተባለ

የናይጄሪያ የመረጃ ሚኒስትር ላአይ ሞሃመድ በሀገሪቱ ትዊተር እንዳይሰራ የተጣለው እገዳ በቅርብ ቀናት ውስጥ ይነሳል ሲሉ አስታውቀዋል።ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ የተጣለው እገዳ መቼ ይነሳል በሚለው ዙሪያ ቁርጥ ቀኑን አልተናገሩም።

የናይጄሪያ የመንግስት ባለስልጣናት እና የትዊተር የስራ ሀላፊዎች በጉዳዩ ላይ ከስምምነት ሲደርሱ የተጣለው እገዳ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ በደቡብ ምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀሱ ተገንጣይ ሀይሎች መንግስታቸው እንደሚቀጣ በትዊተር ገፅ ላይ መልዕክት ማስፈራቸው የውዝግቡ መነሻ ነበር።

ትዊተር የፕሬዝዳንት ቡሃሪን ፁሁፍ ማጥፋቱን ተከትሎ ናይጄሪያ የማህበራዊ ትስስር ገፁ በሀገሪቱ እንዳይሰራ አግዳለች።እግዱ የናይጄሪያ የቢዝነስ ተቋማትን የጎዳ ሲሆን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚያቀጭጭ የሚል ተቃውሞ አስከትሏል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *