መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 6፤2014-እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ቻይናን ለመመከት ያስችላል ያሉትን ስምምነት ፈፀሙ ❗️

እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ቻይናን ለመመከላከል በሚደረገው ጥረት የተራቀቁ የመከላከያ ቴክኖሎጂ እርስ በእርስ ለመጋራት ያስችላል ያሉትን ስምምነት ፈፅመዋል።በአጋርነቱ መሰረት አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኒውክሌር ሀይል የሚሰሩ የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ለመገንባት ያስችላታል።

ስምምነቱ አውኩስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን የኳንተም ቴክኖሎጂ፣የሳይበር እና ሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን ለመጋራት ያስችላል።ሶስቱ ሀገራት ቻይና በኢንዶ ፓስፊክ ያላት ተፅእኖ እያደገ መምጣቱ እያሳሰባቸው ይገኛል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የአውስትራልያ አቻቸው ስኮት ሞሪሰን አዲሱን የደህንነት አጋርነት ማስጀመሪያን በተመለከተ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። በኒውክሌር ሀይል የሚሰራ የባህር ሰርጓጅ መርከብ አቅም አውስትራሊያ እንዲኖራት በጋራ እንሰራለን ሲሉ አስታውቀዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *