መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 7፤2014-በአፋር ክልል በጦርነቱ ሳቢያ 455 ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት ደርሷል !

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ “ህወሓት” ቡድኑ ፣ በፈንቲ ረሱ አራት ወረዳዎች የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም የትምህርት ግብአትና መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ በማውደም ትውልድን የማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ማናጅመንት አባላት በኡዋ ፣ አውራ ፣ ጎሊና እና አውራ ወረዳ ጉብኝት ማድረጋቸው አድርገዋል፡፡

በጉብኝታቸው እንደተመለከቱትም ፣ በግንባታ ዙሪያ በትላልቅ መሳሪያዎች ትምህርት ቤቶች መፍረሳቸውን ፣ አጠቃላይ ግብአቶች ከጥቅም ውጭ መሆናቸውንና የተማሪዎችና አጠቃላይ የትምህርት ቤት መረጃዎች መውደሙን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡

የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ 455 ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት መድረሱን ገልፆ ፣ ለተማሪዎቹን አስፈላጊውን ሁኔታ በማመቻቸት በአስቸኳይ ትምህርት የሚጀምሩበት ሁኔታ እንደሚመቻች አስታውቋል።

ኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *