መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2014-የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሊበራል ፓርቲ በድጋሚ ምርጫ አሸነፈ❗️

በካናዳ ፕሬስ እና በካናዳ የቴሌቪዥን አውታሮች ትንበያ መሠረት የካናዳ ዜጎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሊበራል ፓርቲ ድምፅ መስጠታቸውን ይፋ አድርገዋል። ነገር ግን በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር የሊበራል ፓርቲ አለማግኘቱ ተሰምቷል።

የሊበራል ፓርቲ ከማንኛውም ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ እንዲያገኝ አስቀድሞ ተገምቶ ነበር። የ49 ዓመቱ ትሩዶ በ 2015 ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ማሸነፋቸው ይታወሳል። የጀስቲን ትሩዶ ወላጅ አባት ፒየር ትሩዶ የሊበራል ምልክት ተደርገው ይወሰዱ የነበረ ሲሆን የካናዳ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ ይታወሳል።

የወግ አጥባቂው መሪ ኤሪን ኦትኦሌ ከባለቤቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር ከምርጫው በኃላ ወደ መድረክ በመውጣት የምርጫውን ውጤት መቀበላቸውን ተናግረዋል። ኦትኦሌ የፓርላማ መቀመጫን ቢያሸንፍም የትሩዶ ሊበራል ፓርቲ በስልጣን ላይ እንዳይቆይ ወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው በቂ መቀመጫ ማግኘት ግን አልቻለም።

በርካታ ከሕዝብ አስተያየት የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሊበራሎች በፓርላማ ውስጥ ከፍተኛውን መቀመጫ ያገኛሉ የሚል ቅድመ ግምት ሲሰጥ ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *